Change Languge
ጋለሪ
ሰለ እኔ

Beyond the pit stood the little wedge of people with the white flag at its apex, arrested by these wonders. It does not get any better than this.

GET CONNECTED
የጥበብ መፍለቂያ...

የጥበብ መፍለቂያ...

Aug -24 20 - ፖስት አድራጊው አስተዳዳሪ

“ዕውነት አስቀያሚ ነው፤ የጥበብ አስፈላጊነትም ከእውነታ እንዳንሸሽ ማድረጉ ነው።” ይህ የዕውቁ ጀርመናዊ ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼ ንግግር ነው። ይህ ጥቅስ ከተለያዩ ማዕዘኖች ሊቃኝ ይችላል። ከማዕዘኖቹ ባንዱ በኩል ስናየው ጥበብ ለህይወት ለዛ የመስጠትን ሚና እንደሚጫወት ያሳየናል።

ዓለም ዘላቂነት በሌላቸው ሁነቶች መሞላቷ በራሱ አስቀያሚ ያደርጋታል። በምድር ላይ የምንም ነገር ቋሚ ባለቤት መሆን አለመቻል የያዝነውን እንዳናጣጥምና ባለን እንዳንደሰት እንቅፋት ይሆኑብናል። በዚህም ምክንያት ከሰው ልጆች ከፊሉ አልጠግብ ባይ ይሆንና ሰው የያዘው ሁሉ ያምረዋል። ይህም ስግብግብ ያደርገዋል። ከፊሉ ደግሞ ባለው ነገርም አይደሰትም፣ የሰውንም አይመኝም ባይሆን ሁል ጊዜ ያማርራል፤ ያለቃቅሳል፣ ይተቻል። ነገር ሁኔታውን ለመቀየር አይሰራም፤ አይደክምም። እንዲህ ዓይነቱ ደግሞ ሰነፍ ነው።

ሌላኛው የሰው ክፍል ደግሞ እይታዎችን ይፈጥራል። ነገራቶች ከዕውነታቸው ይልቅ ትርጉማቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ ይጥራል። ሁነቶች በበጎም ሆነ በመጥፎ አኳኋን ቢመጡም አመጣጣቸው ሳይሆን መንሳኤያቸው፣ የመጡበት አቅጣጫ እና በመምጣታቸው የሚከሰተውን ውጤት ይፈልጋል። ከያንዳንዱ ሁነት ቀዳሚና ተከታይ እንደሚኖረው በመረዳት ምናብ ሰጥሞ ከዕውነታው ይልቅ ዕውነታው የመጣበትን መንገድ ይከተላል፣ የስነ ፍጥረትን እምቅ ትርጓሜ ፍለጋ ይወጣል። ይህም ጠቢብ ያደርገዋል።

ጥበብ መነካትን ይፈልጋል። ጥበብ መጥለቅን፣ መጥፋትን፣ ፍለጋ መውጣትን ይሻል። ጥበብን ለማግኘት በመጀመሪያ ከልብ የመነጨ ማጣትን መኖር አለበት። ያላጣ ቢያገኝም ያገኘውን ጸጋ የማወቅ ዕደሉ የጠበበ ነው።  ጥበብ ከጠባብና እጅግ ውስን በሆነው ምድር ውስጥ ሰፊና ወሰን የለሽ ትርጉምን ማግኘት ነው።

የጥበብ ምንጭን ለመረዳት አንድሰው የጎደለውን ማወቅ አለበት፤ የጎደለውን ማያውቅ አሊያ ደግሞ ካለበት አሳልፎ የማይመለከት፣ የማወቅ ረሀብ የሌለበት ሰው ፍለጋ አይወጣም። ስለዚህ ጥበበኛ ጉዳዩ እውነተኛ ለመሆን ሳይሆን ከዕውነት ጎን ለመቆም ነው። ዕውነት ወደመራው ለመሄድና ዕውነት ወደታየበት ልማቅናት ሁሌም ዝግጁ ነው። ምክንያቱም ዕውነት ምን ጊዜም ክሁነት ተነጥሎ የቆመ እንደሆነ ያውቃል።

አስተዳዳሪ

Beyond the pit stood the little wedge of people with the white flag at its apex, arrested by these wonders. It does not get any better than this.

ተዛማጅ ፖስቶች

ሊያመልጦት የማይገባዎት ሌሎች ፖስቶች፡፡

አስተያየት የለም

ላይ የጥበብ መፍለቂያ...

አስተያየት ይተዉ

የእርስዎ አስተያየት ለእኛ ጠቃሚ ነው ፡፡