ቴዎድሮስ ካሳሁን
መጨረሻ ላይ ካሳተመው አልበም ውስጥ የአድማጭን ቀልብ ከገዙ የፍቅር ዘፈኖች መካከል ‘ያምራል’ አንዱ ነበር።
የ ‘ያምራል’ን
የሙዚቃ ውበትና ትርጉም ከሞዛቂው በላይ ለማወቅ መንደርደር የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ ይሆናል። ከአድማጮች አንዱ ከቆመበት ማዕዘን
የዘማውን ፍሰትና የግጥሙን ስሜት እንደሚከተለው አይቶታል…
አንድ በፍቅር የተጨነቀና
የተቃጠለ የውበት ሽኑፍ ያለበትን የሀሴት ስቃይ … ከጥበት፣ ከራስ በመነጠል፣ እና ራስን ከመርሳት ብሎም ከቁጥጥር ውጭ መሆንን
አያይዞ ይገልፀዋል…
"ስፍራ ጠበበው ያንቺ ውበት ፈክቶ ሲታይ…
ደምቆ እንደ ፀሀይ"
በዚህ ስንኝ የተፈቃሪዋ
ውበት የርሱን ከባቢ እንደሞላው ስሞታ በማቅረብ ይጀምራል። ስሞታው ቀላል አይደለም፤ ሰው እንኳን የፀሀይ ብርሀን ላምባም በቀጥታ
ካይኑ ሲገጥም ይቃጠላል። እናም በዚህ ስንኝ የትም ቢሄድ የማያመልጠውና የማይጠለልበት የውበት ፍካት ገጥሞት "ናና እየኝ"
እያለ ውስጠ ልቦናውን ያስገብረው ይዟል። እናም በቃ እጅ ሰጥቷል ምርኮኛም ነው።
ታዲያ ይህን ስንኝ
ዜማ ሲሰጠው ሙሾ እንደሚያወርዱ ሁሉ ዋይ ዋይ ያስብላል። "ያምራል ያምራል… … ያምራለ" በቃ ሙሾ ነው። ለውበት
እጅ የሰጠ አፍቃሪ በዚህ "ዜማ ዋይ ዋይ" ከማለት ውጪ ሌላ አማራጭ አይተውለትም።
ደግሞ በጣም የሚገርመው ቀልቡን እንዲህ ያስረገደውን ውበት የሳለባቸው ቃላት ሁሉ የተፈጥሮ አካላት ናቸው። ውበቱ እርሱ ስላፈቀራት የጎላ እንጂ ከሌላው ሰው የገነነ ተፈጥሮ ስላላት አይደለም። ይህንንም ቅንድብ— በኩል ሲለበጥ የሚሰጠውን ጥቁረት አንስቶ ይጀምርን እንደ ገና ፅድ ላለም መሞሸሯን እስከመለፈፍ ይገፋዋል።
ከዚህም ባለፈ ውቧ
ሶሪት ወፍ ያሸበረቀቸረበትን ላባ ይመዛል። በሶሪት ውብ ወፍ ነች። ላባዋ ግን ይገልጣታል። ልክ የአንበሳ ጎፈሩ፣ የፅጌረዳ ዕንቡጡ
የሸማ ጥበቡ እንደሚታየው ሁሉ የሶሪትም ላባዋ ይጎላል። ሩቢም እንደዛው ነው። ሹም ሲጀምር ከሁሉ የላቀ ክብር አለው፤ በአሁኑ ወቅት
አንድ ሹም ኒሻን እንደሚያደርገው ሁሉ የድሮ የምስራቅ ነገስታት… ከዘውዳቸው ላይ ሩቢ ያስቀምጡ ነበር። ከወርቅም ከአልማዝም ከዕንቁም
የጎላ ጌጥ!
እናም በዚህ ሁሉ
ፍካት ውስጥ ይ ምርኮኛ ማምለጫ አላገኘም። በግራም በቀኝም በኋላም
በፊትም መሄጃ የለውም።
ታዲያ ይህን ሲያውቅ
ተንበርክኮ መሬቱን እየቧጠጠ ደረቱን እየደቃ ሙሾውን ያወረደ ይመስላል።
"ያምራል
ያምራል ዋይ ዋይ!"
"አልሰማ ቢል ልቤ…"
በፍቅር የተነካ
ሰው ይህ ደካማ አፍቃሪ ከልቡ ጋር እንኳን ድርድር መቀመጥ አልቻለም። ይከንፋል ይሄድበታል።
ለነገሩ ውበት ሲጠራ
ማን ሌላን ያዳምጣል?? ለውበት መታዘዝ የሰውልጅ ንጥቀታዊ ምላሽ ነው። የአመክንዮን መልካም ፈቃድ አይጠብቅም። ልብ ለውበትና ለጥበብ
እጅ ይሰጣል። በየሄደበት ሁሉ ውበት ካለ ከሌላው የህይወት ሂደቱ
ሁሉ መነጠሉ አይቀሬ ነው።
በዛብህን
ከደብሩ፣ መጅኑንን ከአቅሉ፣ ሮሚዮን ከህይወቱ የነጠለው። ውበት የት እንደሚጥል አይታወቅምና በዚህ ዜማ ከማንነት የተነጠለ ስብዕናን
ይሰብካል።
አስተያየት የለም
ላይ አልሰማ ቢል ልቤ...