ዕውነትን ከሁነት
የሚለየው ነገር ልክ የጥሬ ዕቃ እና የምርት ውጤት ዓይነት ነው። አንድን ሁነት በምናባችን እና በአዕምሮአዊ አመክኒዮዎቻችን አሳልፈን
ከአካባቢያችንና ከ ባህላችን አንጻር እናሽገውና የራሳችንን ዕውነታ እንፈጥራለን። ስለዚህ እኛ ዕውነት የምንለው የሁነት ተረፈ ምርትን
ነው እንጂ ዕውነትን አይደለም።
እውነት በተቃራኒው
ከኛ አመክንዮም፣ ምናብም፣ ባህል ፣ ዘይቤም የጸዳ ነው። ዕውነት ነጻ ነው። ለዚህም ነው ከዕውነት ጎን መቆም እንጂ ዕውነትን ራሱን
መሆን ማይቻለው።
እናም
ጥበበኛ በሁነትና በዕውነት መካከል ያለውን ልዩነት ተገንዝቦ ሁሉም ሰው ለራሱ ዕውነት ነው ብሎ ያመነውን የሁነት ተረፈ ምርት ወይም
የሁነት ውጤት የተለያየ መልክ በመስጠት ኩሎ እና አሳምሮ ወደ ዓለም መድረክ ያቀርበዋል። የማንም ዕውነት ለማንም ግልጽ ላይሆን
ይችላል፤ ማንም ስለማንም ዕውነት ላይገደው ይችል ይሆናል። ነገር ግን የጥበብ ሰው የሁሉንም ዕውነት ያስውባል። ልክ ግንበኛ ገንብቶ
እንደሚኖረው ሁሉ ጥበበኛም ዕውነታን በማስዋብ ይኖራል። ሰዎችንም
ዕውነታቸውን እንዳይሸሹትና ከዓለም እንዳይቆራረጡ ውበትን ይገልጥላቸዋል።
አስተያየት የለም
ላይ ዕውነትና ሁነት