Change Languge
ጋለሪ
ሰለ እኔ

Beyond the pit stood the little wedge of people with the white flag at its apex, arrested by these wonders. It does not get any better than this.

GET CONNECTED
ሀጫሉ: መኖር ወይስ አለመኖር?

ሀጫሉ ሁንዴሳ ቦንሳ በሙዚቃው ውስጥ በማህበረሰብ ውስጥ የኖረን ቁስል በነዛሪ ድምፁ ያሰረ… አስሮም ጠፈፍ ያደረገ ቄሮ…

Dec -03 20 - ፖስት አድራጊው አስተዳዳሪ

ሀጫሉ: መኖር ወይስ አለመኖር?

 

ሀጫሉ ሁንዴሳ ቦንሳ በሙዚቃው ውስጥ በማህበረሰብ ውስጥ የኖረን ቁስል በነዛሪ ድምፁ ያሰረአስሮም ጠፈፍ ያደረገ ቄሮ

ከአንደበቱ ኩልል በሚሉት ቃላት በህይወቱ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በማህበረሰብ ውስጥ ያለን ህመም ታሞ ያስታመመ አስታሞ ኖሮ ያልጠገበውን ህይወት ገብሮ ከብዙ ከንቱዎች ቀድሞ የተሸኘ ቄሮ

"ምኑን ኖርኩትሲል በደመፀው ሙዚቃ ታሪክን ከህይወት አሰናስሎሥነሠብን በአንድ የፍቅር ረሀብ ውስጥ ደልድሎ በጉሮሮው ስሎ በጥበብ ወዳጆች ላይ ያንቆረው የመለያየት ህመም…  በመሰረቱ ወዳጅ ከወዳጁ፣ ቤተሰብ ከዘመዱ፣ እህት ከወንድሙ፣ ጓደኛ ከጓደኛው፣ በአጠቃላይ ፍቅር የተበተነበትን ሁነት እየጠቀሰ ይቆዝማል

ይህ ጥበበኛ ቄሮ ያፈቀራትን ቀሬ በወደቀበት የጥቅመኞች ግርዶ ምክንያት ናፍቆ ማጣቱን፣ ለፍቶ መገታቱን ካፈቀሩት የመለያየት የሚያመጣውን ማቄምና የሚወልደውን የማይቆም፣ ደርሶ የማግኘት ፍላጎት ያልተረዱት እነርሱ  የለያዩን ቢሆንም እኛ ግን አይገባንም። ሲል ያዝናል

በስንኞቹ የመገፋትንና ራስ ወዳድ ባለጊዜዎች በፍቅር ህይወቱ ላይ የጣሉበትን ጠባሳ ያቀነቅናል። ጥቅም ሲሆን ባህል፣ እሴት፣ እንደ ፍቅር ያሉ ከተራራ የከበዱ የሰውነት መርሆዎች ሳይቀሩ እንደሚገፉና በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሰው እንዴት ኖርኩኝ ሊል ይቻለዋል ሲል በተጠይቅ መንፈስ ውስጥ አድማጩን ይዞት እልም ይላል፤“Diiganii gaara sanaa, Gaara diigamuu hin-mallee,

Nu baasaan addaan baanee, nuu addaan bayuu hin-mallee.”

አፍርሰው ያን ተራራ ፥ ማይገፋውን ነቅንቀው

በኛ መሀል ግርዶ አኖሩ ፥ ከፍቅራችን ጦም አውለው

ሀብታም ሆነን ደጁ ሞልቶ፥ የራበንን ፍቅር ነጥቀው

ለያዩን ሳናስበው  ፥ የውሸት ሳቅ አሳስቀው ...

የሚል የመስላል... በዚህ የቁጭት ዜማ ውስጥ በሚሞዝቀው “ኖስታልጂክ” ወይም ደግሞ የቆየ እና የተቀበረ ስሜትን ፈንቃይ የሆነና በኦሮሚያ ከልል ውስጥ ያለውን የጠለቀ የባህል ትሥሥር በምናብ ቦታው ላይ ወስዶ የሚጥል ነበር፤ በዚህ ዜማ ውስጥ ፍቅር ዋና ነጥቡ ይሁን እንጂ የማህበረሰብ እሴት መበተንን ክለብ በመነጨ የሀዘን ስሜት ይገልጠዋል።

 

በመሰረቱ በስንኞቹ ውስጥ በሃይል ከመገፋት ይልቅ መሰሪዎች አታለውና አሳስቀው በአድር ባይነት የፈጠሩት የጥቅም ሰንሰለት የኦሮሞን ህዝብ እሴት ንደውታል ነው መልዕክቱ።

ታዲያ በዛ ውስጥ ፍቅሩን ማጣቱ ያንገበገበው ወጣት መቼ ይሆን የማይሽ እያለ ... መለያየቱ የናፍቆቱን ነበልባል ይብልጥ እንዳቀጣጠለውና እንደውም ካለርሷ ኑሮ ምኑን ኑሮ ሆነ እያለ ብውስጡ ያነባውን እንባ በዜማ ያቀነቅነዋል...

 

ወደ መጨረሻው አካባቢ በህይወቱ የገጠመውን ባዶነት የገለጸው እንዲህ ሲል ነበር...

“የሌሊት ወፍ ማታ ትላለች ጭው ጭው

ላዋቂ ምስክር ጠባሳ እንኳ ሳይተው

የናፍቆትሽ ጠኔ ደ’ ስታዬን ላጨው...  

ታዲያ ምኑን ኖርኩት ካንቺ ተለይቼ

በላኝ ሀሩር ቁሩ ራቁቴን ቀርቼ

የሩቅ ሀገር ተስፋ መች እንቅልፍ ይሰጣል

የፍቅርሽ ህመሙ ሰባብሮ ይጥላል”

 

እያለ ያነባባቸው ስንኞች በተለይ የቁስሉን ደረጃ ባይነ ህሊናችን እየሳልን አብረን እንድንታመም፣ ከሀዘኑ ጋር አብረን እንድናዝን ያደርገናል። ታዲያ ይህ ቄሮ በዚህ ደረጃ የማህበረሰብን ስሜት ሰቅዞ በመያዝ በታሪኩ ውስጥ በልማት ስም የተፈጸመን በደል በእያንዳንዱ ቤት ምን መልክ እንደያዘ ያሳየበት ታላቅ የትግል ዜማ ተደርጎ እንዲወሰድ ምክንያት ሆናል። ለዚህም ይመስላል በኦሮሞው ብቻ ሳይሆን በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይጠገብ መሄዱ ለዜጋው ሁሉ እጅግ አስደንጋጭና አሳዛኝ ሆኖ ማለፍ የወጣቱ ድምጻዊን በሳልነትና ተወዳጅነት በደማቅ ጽፎታል።

 

*ማስታወሻ ፡ የኦሮምኛ ቋንቋ የግጥም ትርጉሞች በውርስ ትርጉም የተጻፉ ናቸው፤

*የኦርምኛ ዘፈኑን በመተርጎም የተባበረንን ኢብሳ ኢብራሂም በማዕዘን ስም ከልብ እናመሰናለን

 

አስተዳዳሪ

Beyond the pit stood the little wedge of people with the white flag at its apex, arrested by these wonders. It does not get any better than this.

ተዛማጅ ፖስቶች

ሊያመልጦት የማይገባዎት ሌሎች ፖስቶች፡፡

አስተያየት የለም

ላይ ሀጫሉ: መኖር ወይስ አለመኖር?

አስተያየት ይተዉ

የእርስዎ አስተያየት ለእኛ ጠቃሚ ነው ፡፡